የመረጃ እና ድጋፍ ማዕከል ድረ ገጾች የእይታ እና የአእምሮ አካል ጉዳትን ከግምት ውስጥ በማስገባት የተቀየሱ እና የተገነቡ ናቸው ፡፡ በሁሉም ደረጃዎች በድረገጽ ተደራሽነት ላይ ዓለም አቀፍ መመሪያን እና ምርጥ ልምድን ተመልክተናል ፡፡

በተቻለ መጠን በድረገጹ ላይ ያሉትን ሁሉንም ይዘቶች ወደ WCAG 2.1 AA ተገዢነት ማድረስ ዓላማችን ነው ፡፡ ለ WCAG መመሪያዎች ያለንን ተገዢነት የተለያዩ በአውቶማቲክ እና በሰው እጅ በሚዘወሩ የድረ ገጽ እና የሶፍትዌር የተደራሽነት የሙከራ ሥርዓቶችን በመጠቀም  በመደበኛነት እንፈትሻለን ፡፡ የምንፈትሻቸው የፍተሻ ቦታዎች የተወሰዱት የድረ ገጽ ይዘት ተደራሽነት መመሪያዎች 2.1 (WCAG) ከተሰኘው ቴክኒካዊ መስፈርት ሲሆን የታተመውም በ ዓለም አቀፉ ድረ ገጽ ድርጅት ነው:: 

በበርካታ ቴክኖሎጂዎች መፈተሸችንን ለማረጋገጥ የተቻለንን ሁሉ እንሞክራለን ፤ ነገር ግን እያንዳንዱን የአሳሽ ስሪት በእያንዳንዱ የእገዛ ቴክኖሎጂ ስሪት ለመፈተሸ ፣ ወይም በእያንዳንዱ የአሠራር ሥርዓት ስሪት ወይም የሞባይል ቀፎ አይነት ላይ ለመፈተሸ አንችልም። አዳዲስ የእገዛ ቴክኖሎጂዎች ለተጠቃሚው የተሻለ የተደራሽነት ድጋፍ ስለሚሰጡ በጣም አዳዲስ በሆኑ ቴክኖሎጂዎች በመፈተሸ ላይ እናተኩራለን ፡፡ መደበኛ የድረ ገጽ አሳሽ አማራጮችን በመጠቀም የጽሑፎቹን ፣ ቅጾቹን ፣ ማውጫዎቹን ወዘተ መጠን መጨመር ይቻላል።

ሁልጊዜም በድረ ገጹ ተደራሽነት እና አጠቃቀም ላይ ማሻሻያዎችን ለማድረግ እንሰራለን ፤ በተለይም ይዘቱ እና አቅርቦቱ በሶስተኛ ወገን በሚመረኮዝበት ጊዜ፡፡ ድረ ገጻችን በእኛ ቁጥጥር ስር ባልሆኑ ሌሎች ድረ ገጾች ላይ ለሚገኙ ይዘቶች መስፈንጠሪያዎችን ያቀርባል ፡፡ በተቻለ መጠን ከተደራሽነት መመሪያዎች ጋር የሚስማሙ መስፈንጠርያዎችን መምረጣችንን ለማረጋገጥ እንሞክራለን ፡፡ 

ስለ ድረ ገጻችን ማንኛውም አስተያየት እና ምልከታ ካለዎት እባክዎ ወደ  info@safeguardingsupporthub.org  ኢሜል በመላክ ያነጋግሩን ፡፡ 

ለመጨረሻ ጊዜ የዘመነው እ.ኤ.አ. ግንቦት 2020